Friday, August 14, 2015

ፍርድ ቤቱ ለሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የሰጠው የዋስትና መብት በፖሊስ ታገደ

ነኅሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከምርጫው ማግስት ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በፖሊስ ተይዘው ነሃሴ 6 ቀን 2007 ዓ.ም. እያንዳንዳቸው በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ተጠይቀው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ፣ ዋስትናቸው በአቃቤ ህግና በፖሊስ መታገዱን የፓርቲው የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ በአመራሮቹ ላይ ላቀረበው ክስ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ነሃሴ 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ከምርጫው ማግስት እየታደኑ የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ 8 የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን እያንዳንዳቸው የ15 ሺህ ብር ዋስ አቅርበው እንዲፈቱ የወሰነ ሲሆን ሁለቱ ወዲያውኑ ወጥተዋል፡፡ ይሁንና የዋስትናው ገንዘብ እስኪሞላላቸው እስር ቤት የቆዩት 6ቱ አመራሮች ማለትም ልዑልሰገድ እምባቆም ፣ ፋንታሁን ብዙአየሁ፣ መንግስቴ ታዴ፣ አዳነ አለሙ፣ መምህር ስማቸው ምንይችልና አበባው አያሌው ትናንት ነሃሴ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. የክልሉ አቃቤ ህግና ፖሊስ ለማረሚያ ቤቱ ባቀረቡት ጥያቄ ዋስትናቸው መታገዱ ታውቋል፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ዋስትናቸው የታገደው ገንዘቡን ካስያዙ በኋላ መሆኑንም ነገረ -ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡
Source : http://ethsat.com/amharic/%e1%8d%8d%e1%88%ad%e1%8b%b5-%e1%89%a4%e1%89%b1-%e1%88%88%e1%88%b0%e1%88%9b%e1%8b%ab%e1%8b%8a-%e1%8d%93%e1%88%ad%e1%89%b2-%e1%8a%a0%e1%88%98%e1%88%ab%e1%88%ae%e1%89%bd-%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%8c%a0/

No comments:

Post a Comment